ማነው ከኦሮሞ በላይ ኢትዮጵያዊ ??

FB_IMG_1587310889249

እኛም ስለ ኦሮሞ ልንጽፍ ተነሳን ፦ ኢትዮጵያዊነትን ለኦሮሞ ህዝብ አታስተምሩትም ያስተምራችኋል 💪💪

ኦሮሞ ከኢትዮጵያ ህዝብ ገሚሱን የሚሸፍን ፥ ከሰሀራ በታች ከሚገኙ የአፍሪካ ሀገሮች ውስጥ የቀዳሚው ካሌንደር ባለቤት (በናሳ ሳይንቲስቶች የተረጋገጠ) ፤ በዓለም ከግሪክ አቴና ዴሞክራሲ በሁሉም መስክ የሚልቅ ፦ ስልጣን ርስት ሳይሆን በየ8 ዓመቱ የሚለዋወጥበት ፥ መሪዎቹ በችሎታቸው የሚመረጡበት ፤ ለፓርላማው ታዛዥ የሆኑበት ፥ ከአባ ገዳው ጀምሮ first among equals የተለየ ጥቅም የማያሰጥ ፥ ፓርላማው ከፍተኛ የስልጣን አካል የሆነበት egalitarian ፤ ባሪያ የሌለበት freedom to all regardless of wealth and hereditary kinship ፥ ልመና የሚያሳፍር በመሆኑ እጁን ለስራ እንጂ ለስጡኝ የማይዘረጋ dignified existence ፤ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ መለያ ባንዲራ ከሮም እስከ አሜሪካ ያውለበለቡ ጀግኖች መፍለቂያ patriotic in actual sense ፤ በአገር ውስጥ አርበኝነትም ሆነ በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ጀግና መሪዎች የነበሩት ፤ በአፍሪካ የቀንድ ከብት አንደኝነታችን መሰረት ፥ የኢኮኖሚ ዋልታ ቡና ብለን ብንዘምር የአንበሳውን ድርሻ የሚይዝ ፤ የራሱ Pope አባ ሙዳ ፥ ወንድና ሴት ካህናት ቃሉና ቃሊቲ ያሉት ፤ አዋሽ ፥ ገናሌ ፥ ዋቢሸበሌ ፥ ዳዋ ፥ ጊቤና ሌሎች ወንዞች የሚገማሸሩበት ፥ ውበቱና እንግዳ ተቀባይነት ባህሪው እንደ ገባር ወንዝ እየጠራቸው ከውስጥም ከውጪም የሚፈሱ ጅረቶችን ባህር ሆኖ የሚቀበል ፥ ወደ ሌሎች የማይፈስ ፥ በኢትዮጵያ ታሪክ በሩጫ አበበ ቢቂላ ፥ በዘፈን ጥላሁን ገሰሰ ፥ በሳቅ በላቸው ፥ በስነ ጽሁፍ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ፥ በውበት ውቢት አመንሲሳ ፥ በወርቅ አዶላ ወለጋ ፥ በዴሞክራሲ ፥ በሀብት ፥ በብዛት ፥ በእምነት ፥ በካሌንደር +( በአጠቃላይ የማይልቅበት ዘርፍ የሌለ) ፥ ታላቅ የርብርብ ማዕከል የሆነ ፤ ከሁሉም በመቀላቀል ለከፈለው ታላቅ ዋጋ የቀልደኞች አፍ መፍቻና መክፈቻ የሆነ ታላቅ ህዝብ ነው ።
በታሪክ አወዛጋቢው መሪ አፄ ምኒልክ የጀግንነቱን ልኬት ተገንዝበው ፦ የጦር ሚኒስትራቸውን ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ አባ መላ ፥ የጦር መስፋፋት ሚኒስትራቸውን ጎበና ዳጬ ፥ ሠራዊታቸውን በኦሮሞ ጦር መገንባታቸውን መካድ አይቻልም ፤ መኮንን ጉዲሳ ፥ አብዲሳ አጋ ፥ ባልቻ ሳፎ ፥ ታደሰ ብሩ ፥ አበበ አረጋይ ፥ በቀለ ወያ ፥ ገረሱ ዱኪ ፥ አብቹ … ወዘተርፈ ጀግኖችን መጥቀስ እንችላለን ። እስኪ በጣሊያን ጊዜ ተቀዳሚ ባንዳዎች እነማን ነበሩ? አንድነት ይበጃል ብለን ዝም ማለታችን ታሪክ የሌለን ካስመሰለንማ ገና ብዙ ምንጽፈው አለን ። የፍቅር እንጂ የግጭት መንስዔ አይደለንም ። ማንም ኢትዮጵያዊነትን አልሸለመንም ፥ አይሸልመንም ፥ ዕውቅናም አንጠይቅም ። እኛ አንጋፋ ቀዳሚ ኢትዮጵያውያን ነን ። የማንም ውለታ የለብንም ። በአድዋ ተራሮች ደማችን ተንዠቅዥቋል ፥ በሶማሊያ ወረራ ወቅት ከማንም በላቀ ሁኔታ ደማችን ፈሷል ፤ ከማንም በላይ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ደም እኛ ውስጥ አለ ። ኦሮሞ ትልቁ የማቅለጫ ገንዳ ግንድም ነው ።

Ilma Dasu Odaa, Ijoollee Booranaa
The pictures and text were taken from different sources.
Mengistu Gudissa :ይጨመርበት
ገበየሁ ቢምት ተተካ ባልቻ
መድፍ አገላባጭ ብቻ ለብቻ
የአደዋው ጀግኖች ሳይንቲስቶቹ እነ ፕ ር አክሊሉ ለማ ደበላ
እነ ፕር ገቢሳ ኤጀታ ሰማዕታት ቱ ጳጳስ አቡነ ጴጥሮስ .መገርሳ በዳሳ የክብር ዶክተር ወይዘሮ አበበች ጎበና የኢትዮጵያ ልጆችን ከአብራካቸው እንደ ወጡ አቅፈውና ደግፈው ያሳደጉ እና ብዙ ሌሎችም ታዲያ ከዚህ ህዝብ የወጡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጀግኖች ስናስታውስ ኢትዮጵያዊነትን በደሙና በአጥንቱ ካነፀ በኃላ ይሰብካል እንጂ ምን ይሰበካል?የሆነውንነና የሚኖረዉን ኢትዮጵያዊነት ማነው የሚነግረው? በኢትይኦጵያ ታሪክ ብዙ የኦሮሞ ብሄራዊ ጀግኖች ተፈጥረዋል ።

የሰሩትም የተሰዉትምበኢዮጵያዊነት ነዉ ኢትዮጵያዊ ነት ከሱም ወዲያ ላሳር።

Credit ~taye bogale arega

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s